ደብረ           ናዝሬት
 

ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። 

                             2ኛ ተሰ  3፥ 6

 

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፣ ያድናቸውማል

 

መዝ 33፥7

 

መንፈሳዊ    መጽሐፍ በገበያ ላይ

የሃይማኖት ሰው በሚል ርእስ በመልአከ ገነት በለጠ ይረፉ አዘጋጅነት የቀረበ አዲስ መጽሐፍ ከነሐሴ 9 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ በገበያ ላይ ዋለ መጽሐፉ በተለይ የሰው ልጅ በሃይማኖት ሲኖር ምን ምን ተግባራትን ማከናወን እንዳለበት እና ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ምን ማድረግ እንዳለበት ያስረዳል

ከዚህም በተጨማሪ

ስለ ጾም

 ስለ ንስሃ

    ስለ ምጽዋት

     ስለ ሃይማኖት

  ስለ ጸሎት

   ስለ አስራት

  ስለ ፍቅር

      ስለ ምግባር  

 ወ ዘ ተ , , , , በሰፊው ያስረዳል

  እንዲሁም መጽሐፉን የሚያነቡ ሁሉ መንፈሳዊ እውቀታቸውን የሚፈትሹበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችን ይዟል መጽሐፉን ገዝተው በማንበብ መንፈሳዊ ህይዎትዎን ያጠንክሩ  ዋጋ  $10

 

በደብራችን የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ ያገኙታል

 

በጅምላም ሆነ በነጠላ ለመግዛት  

 

314 874 5413

202 384 0645

tewahido11@yahoo.com

 

ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።   2ኛ ተሰ  3፥ 6

በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።  መዝ 44፥9

ወደ እኔ 

         ማቴ. 11፥28


እግዚአብሔር ሁሉን አዘጋጅቶ በመጨረሻ ለፈጠረው ለሰው ልጅ ያላደረገለትና ያልሰጠው ነገር የለም፡፡

ንሰሐ ግቡ ከኃጢአታችሁም ተመለሱሕዝ. 146

 

ንስሐ ነሰሐ ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ነው፡፡ የቃሉ ፍቺ ሐዘን፣ ጸጸት፣ ቁጭት፣ ምላሽ፣ መቀጮ፣ ቅጣት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሳ ማለት ነው፡፡ 

         ጾመ ሐዋርያት

በየአመቱ በዕለተ ሰኑይ ብቻ (ሰኞ ቀን ብቻ) የሚጀምሩ ሦስት አጽዋማት አሉ፡፡ እነርሱም ዓቢይ ጾም፣ ጾመ ነነዌ እና ጾመ ሐዋርያት ናቸው፡፡ እነዚህ አጽዋማት ምን ጊዜም ቅበላቸው እሁድ ሲሆን የሚገቡት ደግሞ ሰኞ ቀን ነው፡፡ በየትኛውም አመት ይህን ዕለት አይለቁም፡፡

 

ስለዚህ የ2003 ጾም ሐዋርያት ሰኔ 6 የፊታችን ሰኞ ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በየግላችንም ያጋጠሙንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ውጊያዎች በማሰብ ድል የምናደርግበትን ኃይል ፈጣሪያችን ይሰጠን ጾሙን ከወትሮው በበለጠ ጥንቃቄ ልንጾመው ይገባናል፡፡

በዓለ መከር .በዓለ ሠዊት .በዓለ ኀምሳ

በብሉይ ኪዳን ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሱባኤ (ዐርባ አጠኝ ቀናት ካለፉ) በኋላ በሃምሳኛዉ ቀን በዓለ መከር ወይም በዓለ ሠዊት ይከበራል፡፡/ዘጸ 2316 ዘኁ 28 26/ ይህ በዓል ከስሙ እንደምንረዳዉ አማኞች ወይም እሥራኤል ከአዝመራቸዉ ቀድሞ የደረሰዉን (ቀዳምያቱን) ይዘዉ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡበትና እርሱንም የሚያመሰግኑበት በዓል ነዉ፡፡ ምሳሌነቱም ከእግዚአብሔር ርቆ ከኖረዉ የሰዉ ዘር የሚጠበቀዉን ቀዳሚ ፍሬ ማመላከት ነበር፡፡

በአለ ጰራቅሊጦስ

ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው ይህ በዓል ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱንአንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እሰከ ትለብሱ ኃይለ እም አርያምሉቃ 2449

ብሏቸው ዐረጎ ነበር፡፡ተናግሮ  የማይስቀር  ምሎ የማይክድ ነውና ባረገ 10ኛው በተነሣ 50ኛው ቀን ጰራቅሊጦስን ሰዶላቸዋል ፡፡

 

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ

እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ .መዝ.፸፯፥፷፭ 
                                                                         በዲ/ ሄኖክ ኃይሌ 

‹‹እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላው ገደለ የዘላለም ኀሣር ሰጣቸው፡፡››    መዝ.፸፯፥፷፭

       እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር ፈርኦንን ከነሠራዊቱ በባሕረ ኤርትራ አስጥሞ ከባርነት ነጻ ካወጣቸው በኋላ በምድረ በዳ እንደበጎች እየመራ ርስቱን በገመድ ካካፈላቸው በኋላ ያደረገውን ረስተው አሳዘኑት፡፡ ‹‹አስቆጡት ምስክሩንም አልጠበቁም እንደ አባቶቻቸውም ከዱ እንደ ጠማማ ቀስትም ተገለበጡ በኮረብታ መስገጃዎቻቸውም አስቆጡት በተቀረጹ ምስሎቻቸውም አስቀኑት፡፡ እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቆጣ እስራኤልን እጅግ ናቀ የሴሎምን ማደሪያ ተዋት›› /መዝ. ፸፯፥፶፯/ በሕዝቡም ላይ ተቆጥቶ በጠላት እጅ እንዲወድቁ አደረገ፡፡ በዚህ ቁጣ የተነሣ ርስቱን ቸል አላቸው ጎልማሶቻቸውን እሳት በላቸው ካህናቶቻቸው በሰይፍ ሲወድቁ ያለቀሰ የለም፡፡ ለቅሶ በሁሉም ቤት ነበርና አጽናኝ ለመሆን የሚችል ማንም አልነበረም፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ለፍጥረቱ የሚራራ አምላክ በምርኮ የወደቁትን ሕዝቡን አሰበ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይንም ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው ጠላቶቹንም በኋላው መታ የዘላለም ኀሣር ሰጣቸው፡፡››


                  ቀዳሚት ስዑር

ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈበት ዕለት ነች፡፡ ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት እግዚአብሔርን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ ስላረፈበት ሰንበት ዐባይ /ታላቋ ሰንበት/ ትባላለች ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዘፍ.13፡፡

ሆሳዕና

«አንች የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ ንጉሥሽ በእህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል» ተብሎ እንደተጻፈ ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አግኝቶ በእርሱ ተቀመጠ ዮሐ.1215፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ አስቀድሞ 1400 ዓመታት በፊት እግዚአብሔር በአብርሃም የእምነት ቃል ኪዳን ሕዝቡ ያደረጋቸውን እስራኤላውያንን በጽኑ ክንድ ከባርነት ቀንበር አውጠቶ ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን አምድ እየመራ በመገናኛዋ ድንኳን ውስጥ አድሮ እርሱ ንጉሣቸው ሆኖ እነርሱ ደግሞ ህዝቡ ሆነው በምድረ በዳ መራቸው፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከነዓንም አገባቸው፡፡ 
                      ኒቆዲሞስ
       (የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡

ትርጉም: ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምሕር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።

                ገብር ኄር

       (የአብይ ጾም 6ኛ ሳምንት)

    
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
መኑውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ፡፡

ትርጉም: ጌታው በመልካም ሥራ የሚያገኘው በሐብቱ ኹሉ ላይ የሚሾመው፤የታመነ በጎ አገልጋይ ማን ነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለኾንህ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ይለዋል፡፡


መልዕክታት
2ኛ ጢሞ.2÷1-15 ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡
1ኛ ጴጥ.5÷1-11  እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡  
ግብረ ሐዋርያት
የሐዋ.1÷6-8 እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"
ምስባክ

መዝ. 39÷8   "ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"

ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ

ወንጌል
ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ”
ቅዳሴ
ዘባስልዮስ

        ደብረ ዘይት

 

 

ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።

                                

              መጻጉዕ

 < ተንሥዕ ንሣዕ ዓራተከ ወሑር >  ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ > /ዮሐ.58/

                        ምኩራብ

 

ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ»

ቅድሰት - የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት

. ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን  ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያ ሥራ ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

አቢይ ጾም ,ጾመ ሁዳዴ, የመጀመሪያውን ጾም የምንቀበልበት ሰንበት ወይም ቅበላ የተባለው እሁድ  ዘወረደ ወይም ,ሙሴኒ,

      አቢይ ጾም   በዲ/ ዘላለም ቻላቸው

 

                                                                          

አንድ ሰው ለጉዞ ሲነሣ ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለበት፡፡ በዐቢይ ጾምም እንዲሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ዐቢይ ጾም መንፈሳዊ ጉዞ ነው፤ መድረሻውም ትንሣኤ ነው፡፡ ለእውነተኛው መገለጥ ለፋሲካ መሟላት የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡ ስለዚህ በጣም አስፈላጊ የሆነና ስለ ክርስትና እምነታችንና ሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ስለሚገልጥልን ይህን በዐቢይ ጾም እና በትንሣኤ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት በመሞከር መጀመር አለብን፡፡

                      የነነዌ ሰዎች

                  የንስሐ ምስክሮች    

        የነነዌ ጾም ከሰባቱ የቤተክርስቲያን አጽዋማት አንዱና የዐቢይ ጾም ማዘጋጃ ደወል ነው፡፡ ይህ የነነዌ ሰዎች የንስሐ ታሪክ በቤተክርስቲያናችን በጣም ታላቅ ዋጋ ያለውና የራሱ መዝሙር የሚዘመርለት፣ ቅዳሴ የሚቀደስበት ታላቅ መታሰቢያ ያለው ታሪክ ነው፡፡ ራሱ ጌታችንም የነዌ ሰዎችን የንስሐ ታሪክ በመጥቀስ አይሁድን ገስጾበታል፤ በፍርድ ቀንም በዚያ ትውልድ ዘንድ እንደሚፈርዱበት ተናግሯል፡፡ ይህም የሆነበት የነነዌ ሰዎች 

ቅዱሳን መላእክት

ቅዱስ ማለት የተለየ ፣ የተከበረ ፣ የተመሰገነ ፣ የተመረጠ ማለት ነው  ቅዱሳን መላእክት ስንልም ከርኩሳን መላእክት የተለዩ የተከበሩ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ማለታችን ነው  ተጨማሪ ያንብቡ